by admin | Mar 26, 2024 | History
(more…)
by admin | Mar 23, 2024 | Uncategorized
(more…)
by admin | Mar 20, 2024 | Amharic, News
20-03-2024 - ፓሪስ
ላለፉት ዘጠኝ ወራት የቲም ኢትዮጵያ 2024 ፓሪስ አብይ ኮሚቴን በዋና ሰብሳቢነት ሲያገለግሉ የቆዩት በዩኔስኮ
የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ የሥራ ቆይታቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ
መመለሳቸውን ተከትሎ በኮሚቴ አባላቱ ላበረከቱት አስተዋፅዖና በጎ አገልግሎት የምስጋና እና የሽኝት
ፕሮግራም ተካሄደ።
በርካታ የቲም ኢትዮጵያ 2024 ፓሪስ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በተካሂደዉ በዚሁ ልዩ ዝግጅት ላይ ከኮሚቴው
ምስረታ ጀምሮ ዶ/ር ጥላዬ ጎልህ ሚና የነበራቸዉ መሆኑ ተጠቅሷል። በመሆኑም በፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ
ከዚህ ቀደም ከተሳተፉባቸው ኦሎምፒክ በተለየና ባህላዊ እና ታሪካዊ ይዘቶች የተካተቱበት ልዩ ልዩ ኩነቶች
የሚካሄድበት ዝግጅት ለማካሄድ በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት በዕቅድ አወጣጥ፣ በማስተባበር፣ በአመራር
እንዲሁም ልምድ እውቀታቸውን በማካፈል እስካሁን ድረስ ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋፅዖ የኮሚቴ አባላቱ
ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ምንም እንኳን ዶ/ር ጥላዬ የሥራ ቆይታቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ተመላሽ ቢሆኑም፣ ባሉበት በኮሚቴው
የተጀመሩ ሥራዎችን ከግብ ለማድረስ በማስተባበር፣ በሃሳብና በምክር ለኮሚቴው የሚሰጡትን ድጋፍና
አገልግሎት እንዲቀጥሉ በኮሚቴ አባላት ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ተወዳዳሪዎች ስኬታማ ውጤት የሚያመጡበት ኦሎምፒክ እንዲሁን መልካም
ምኞታቸውን የገለጹት ዶ/ር ጥላዬ በተቋቋመው የቲም ኢትዮጵያ ኮሚቴ ሥርም በተለያዩ ዝግጅቶች
የኢትዮጵያን ባህልና የኦሎምፒክ ታሪክ አድምቆ ፓሪስ ላይ ለማሳየት በኮሚቴው እና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ
ኮሚቴ የታቀዱት ሥራዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ አባላቱ ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
ከኮሚቴው ጋር በነበራቸው የሥራ ቆይታም በርካታ መሠረታዊ መሰራታቸዉን በማዉሳት የአባላቱን ትጋትና
ቁርጠኝነትንም አድንቀዋል። በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገር መፍትሄ የማጀት
አስፈላጊ መሆኑንም ዶ/ር ጥላዬ ጠቁመዋል።
በቀጣይም ከቲም ኢትዮጵያ ኮሚቴ ሆነ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር የሚኖራቸዉ የስራ ግንኙነት
የማይቋረጥ መሆኑና ባሉበት ድጋፋቸዉንም ሆነ ልምዳቸዉን ከማካፈል ወደ ኋላ እንደማይሉ በዚሁ ልዩ
ዝግጅት ላይ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ 2024 ፓሪስ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን
(more…)
by admin | Mar 12, 2024 | Amharic
የፓሪስ 2024 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን እና የቲም ኢትዮጵያ 2024 ፓሪስ ኮሚቴ አባላት መካከል ዉይይት ተካሂደ
(more…)