የፓሪስ 2024 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን እና የቲም ኢትዮጵያ 2024 ፓሪስ ኮሚቴ አባላት መካከል ዉይይት ተካሂደ

Date March 12, 2024 ፓሪስ

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ እና ፖራለምፒክ የኢትዮጵያን የኦሎምፒክ ተሳታፊ የልዑካን ቡድንን ለመቀበል እና ለመደገፍ በአዘጋጅዋ በፈረንሳይ ሀገር እና በሌሎችም በ አውሮፓ ሀገራት ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመዉ የቲም ኢትዮጵያ 2024 ፖሪስ ኮሚቴ አባላት ፣ በፈረንሳይ የ ኢትዮጵያ ኢምባሲ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪስ 2024 ልዑካን ቡድን ጋር በፓሪስ በኦሎምፒክ ዝግጅት ወቅት ለ ልዑካን ቡድኑ በሚደረገዉ አቀባበል እና የተለያዩ ዝግጅቶችን በተመለከተ በኮሚቴዉ በቀረበዉ ረቂቅ እቅድ ፓሪስ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በዚሁ የውይይት መድረክ ላይም ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አቶ ቢልልኝ መቆያ እና ዶ/ር ኤደን አሸናፊ የአብይ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ዶ/ ር ጥላዬ ጌቴ በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ ሲገኙ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ማህሌት ሃይሉ ተሳትፈዋል።

team ethiopia 2024 paris

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከተሳተፈችባቸዉ የኦሎምፒክ ዝግጅቶች የፓሪሱን የ 2024 ኦሎምፒክ በተለየ እና ባማረ ሁኔታ ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት እንዲሆን እና በተለየ መልኩ ለማካሄድ ከወዲሁ በቲም ኢትዮጵያ 2024 ፓሪስ አብይ ኮሚቴ ስር 6 ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል። በፓሪሱ ኦሎምፒክ ወቅት ሆነ አስቀድሞ ለሚደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች ኩነቶችን ፣ ቀደም ብለዉ በሚሰሩ የቅስቀሳ ፣ ንቅናቄ ስራዎች ፣ ሀገርን የማስተዋወቅ እንቅስቃሴዎች ፣በፋይናንስ እና ሀብት አሰባሰብ እንዲሁም የመገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ላይ ባቀረቧቸው ረቂቅ እቅድ አፈፃፀም ላይ ይሁንታ ባገኙና ማረሚያ የሚያስፈልጋቸዉ ዕቅዶች ላይም ዉይይት ተደርጓል። ለልዑካን ቡድኑ ከኮሚቴዉ አባላት ለቀረቡላቸዉ ሌሎች ጥያቄዎችም መልስ ተሰጦባቸዋል።

የተወያዩባቸዉ እቅዶች በቅርቡ በስራ ላይ እንዲዉል ና የፓሪሱ ዉይይት ከተጠያቂነት ጋር በተያያዙ ማን ምን ይሰራል በሚለዉ ግልፅ ምላሽ የተሰጠበት ነዉ ሲሉ በኢ.ኦ.ኮ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የቴክኒክ ክፍል ና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ቢልልኝ ተናግረል።

በፓሪስ 2004 ኦሎምፒክ በአዉሮፓም ሆነ ከአሜሪካና ከተቀረዉ አለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ደጋፊዎች ፓሪስ ላይ በመገኘት ኢትዮጵያዉያን ተወዳዳሪዎችን እንዲደግፉ ፣እንዲሸልሙ ና እንዲዝናኑ አቶ ቢልልኝ መልዕክታቸዉን ያስተላለፉ ሲሆን ለሌላዉም አፍሪካዉያንም በኢትዮጵያዉያ ሰንደቅ ስር እንዲሰባሰቡ የሚደሰቱበትን ዝግጅት መታቀዱንና የኮሚቴዉ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ዉይይቱ እጅግ የተሳካ እና ከጠበቁት በላይ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የኢ.አ.ኮ አቃቢ ነዋይ ና የፓሪስ 2004 ኦሎምፒክስ የፋይናስ ጉዳዎች አላፊ የሆኑት ዶክተር ኤደን አሸናፊ ስለ ውይይቱ በተመለከተ እንደተናገሩት የፓሪስ ኮሚቴ ኢትዮጵያዉያ ኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን የተሳካና የተለየ ቆይታ እንዲኖራቸዉ እያደረገ ያለዉ ቅድመ ዝግጅት የሚስደንቅ ነዉ ብለዋል።

ዶ/ር ኤደን ጨምረዉም ፓሪስ 2024ኦሎምፒክስ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ተሳትፎ እና ልዮ ልዮ መረጃዉች የሚስጥ ይፋዊ ድረ ገፅ እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችይፋ መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ እና ፖራለምፒክ ኮሚቴ እና በፓሪስ ቲም ኢትዮጵያ 2024 ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በጋራ የሚጠቀሙበት ይፋዊ ድረ ገፅ እና የበየነ መረብ ገፆች ከሆኑት ፌስቡክ የ “ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ቲም ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን” በሚል ስያሜ መሰየሙም ታዉቋል።

“ኢትዮጵያ ትወዳደር ተወዳድራም ታሸንፍ “ የሚለዉ መሪ ቃል ለ ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ በመሪ ቃልነትም መመረጡ ይፋ ሆኗል።

team ethiopia 2024 paris

በተያያዘም ከዚህ ቀደም የኢትዬጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን ተወካዮች እና ከዚሁ ለፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ከተቋቋመዉ ኮሚቴ ጋር ሲማከሩ ይህ ሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ሲታወቅ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በሆኑት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የሚመራዉ ልዑካን ጋር ባለፈዉ እ.ኤ.አ ሰኔ ወር 2023 ፓሪስ ላይ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በመቀጠልም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ደራቱ ቱሉ የተመራዉ ሌላዉ የልዑካን ቡድን በፓሪስ በነበረዉ ቆይታ ከቲም ኢትዮጵያ 2024 ጋር ውይይቶችን ማካሄዱ ሲታወቅ በወቅቱም ከፓሪስ አቅራቢያ ከሚገኘዉ ከ አንቶኒ ከተማ አስተዳደር ጋር ለ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ተወዳዳሪዎች ቅድመ ዝግጅት እና ልምምድ የሚያደርጉበት የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል በነፃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ከአንቶኒዉ ከተማ ከንቲባ ዣን-ኢቭ ሴና ጋር መፈረማቸዉ ይታወሳል።

team ethiopia 2024 paris

@ Team Ethiopia 2024 Paris, Media & Communication

Join Team Ethiopia 2024 
admin
Author: admin